ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ 18ኛውን የነፃ ልብ ቀዶ ጥገና በዛሬው እለት አከናወነ::
በ17ኛው የልብ ቀዶ ጥገና አሳዛኝ ውጤት ከደረሰብን ስብራት ወጥተን እነሆ ዛሬ 18ኛውን የተሳካ ውጤት ለማየት በቅተናል:: የዚህ ወጣት አንደኛው የግራ ልብ በር (mitral valve) አራት ሰአት በፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና የተቀየረለት ሲሆን ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚመጣ የልብ በር በሽታ Rheumatic Heart Disease (RHD) ለብዙ አመታት ሲሰቃይ ነበር::
የህክምና እቃ ወጪውን ሙሉ በሙሉ የሸፈኑት አንድ ግለሰብ ሲሆኑ; ይህ ሩህሩህ, አዛኝና ልበ ቀና ግለሰብ ከዚህ በፊትም የአንድ መምህር ልጅን የይህወት አድን የልብ ቀዶ ጥገናን እንድንሰራ ሙሉ ወጪ መሸፈናቸው ይታወሳል::የአገር በቀል የነፃ ልብ ቀዶ ጥገና አድራጊ ቡድንም ይህንን ከባድ ሀላፊነት በድ ል ተወጥቷል:: 19ኛውና 20ኛም ይቀጥላል::
ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ , Healing Valves Ethiopia (HVE) የአዲግራትን ጥሪ በድል አስተናገደ