19ኛውን ስራችንን በጦርነቱ ለተጎዱ ህፃናት;
ት/ቷን ከ5ኛ ክፍል ለማቋረጥ የተገደደችው በቶንሲል ምክንያት የሚከሰተው የልብ በር በሽታ ለልብ ድካም ዳርጎ ላለፉት አምስት አመታት በሙሉ አላራምድ ሲላት ነበር::
አምስት ሰአት የፈጀው ይህ የልብ ቀዶ ጥገና አንዱን የግራ የልብ በመቀየር (mitral valve replacement) እና አንድ የቀኝ የልብ በር በመጠገን (tricuspid valve repair) የተጠናቀቀ ሲሆን, አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ነቅታ በመልካም ሁኔታ ላይ ትገኛለች::
የህክምና እቃ ወጪውን ሙሉ በሙሉ የሸፈኑት አንድ ግለሰብ ሲሆኑ; እንኳንም ተዋወቅን ከማለት ባሻገር, የአገር በቀል የነፃ ልብ ቀዶ ጥገና አድራጊ ቡድንም ይህንን ከባድ ሀላፊነት በድ ል ተወጥቷል:: 20ኛውም ይቀጥላል:
ክትፎ ችርስ;