ASDENAKI – HVE 5th patient

ASDENAKI – HVE 5th patient

በዛሬው እለት (12,18,21) አስደናቂ የተባለ የ18 አመት ወጣት እንደስሙ አስደናቂ እና ያልተለመደ የልብ ቀዶ ጥገና በስኬት ተካሄደለት:: በዚህ አራት ሰአት በፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና ከግራ ልብ (Left ventricle) ወደ Aorta መውጫ በር ላይ ተከስቶ የነበረው መለጠጥ ( right coronary cusp aneurysm) በማውጣት እና በመጠገን የልብ በርን መቀየር ሳያስፈልግ በተሳካ ጥገና ተጠናቋል:: አስደናቂም የልብን ስራ ተክቶ ከሚሰራው ማሽን ያለችግር መላቀቅ ችሏል:: በአሁኑ ሰአት በራሱ እየተነፈሰ ሲሆን የልብ ምቱም ከፔስሜከር ባትሪ ነፃ ሆኖ በራሱ እየመታ ይገኞል::
HVE የበጎ ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አድራጊ ቡድን ለአስድናቂ በፍጥነት እንዲያገግም እና በሰላም ከቤተሰቡ ጋር በቶሎ እንዲቀላቀል ይመኞል:: ይህን ድንገተኞ የልብ ቀዶ ጥገና እንዲሰራ በገንዘብ ለረዳችሁን ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ::

Thanks to HVE today (12|18|21) an 18 Years old boy from Hawassa, Bensa,underwent one of the rarest open-heart surgery successfully. In a four hour taking open-heart surgery voluntary local team of Ethiopia reliefed LVOTO caused by a huge RCC aneurysm. The aneurysmal sac abating the IVS was excised out and the opening to the aneurysm on the RCC was closed using a patch without a need to replace the valve. The surgery went smooth and patient separated from bypass machine safely. Asdenaky is breathing by his own. And his heart is beating regularly without a pacing box support.
We wish Asdenaky a fast recovery and reunite with his family in full health in short time. We would like to extend our heart felt appreciation to those beautiful soul and heart who helped us financially to underwent this surgery.