BLEN – HVE 21st  patient

BLEN – HVE 21st patient

የ8 አመቷ ታዳጊ 21ኛዉ የHealing Valves Ethiopia (HVE) የነጻ የልብ ቀዶ ጥገና ተጠቃሚ ሆነች። ለመጀመርያ ጊዜ የአ/አ ነዋሪን ተጠቃሚ ያደረገው ድርጅታችን; በቶንሲል ምክንያት በሚከሰት የልብ በር ህመም(Rheumatic heart disease) ለተደጋጋሚ የልብ ድካም እየዳረገ የሆስፓታል አልጋ ቤቷ እስኪመስል አድርጏ ከቤቷ አርቋት ነበር።
በሀገራችን ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ የሚጠይቀውን ይህን ቀዶ ጥገና ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ለሚኖሩት የታዳጊዋ ቤተሰቦች የማይታሰብ ነበር። ወደ HVE ቢሮ በኦክስጅን ላይ ሆና የደረሰችው የ8 አመቷ ብሌን በዛሬዉ እለት 5 ሰአተ በፈጀው የልብ ቀዶ ጥገና የተሳካ ህክምና ተደርጎላታል።
በከፍተኛ ደረጃ የተጎዳውን አንድ የግራ የልብ በር (Severe mitral valve regurgitation plus giant left atrium) በስኬት በመጠገን (Mitral Valve Repair plus Left Atrial reduction) የሀገር በቀል የHVE የበጎ አድራጊ ቡድን የተጣለበትን ሀላፊነት በድል ተወጥቷል።
ለመላው የHealing Valves Ethiopia ቤተሰቦች እንኳን ደስ አለን።