የገና ስጦታ በገና ማግስት ማግስት ከሂሊንግ ቫልቭ
የኮሌጅ የIT ትምህርቷን ገንዘብ ቢቸግራት በጐዳና የቡና ጠጡ ገቢ መቀጠል ብትችልም ልቧን የያዘው በሽታ ግን መላ ያጣችለት ችግር ከመሆንም አልፎ ከትምህርቷም ከቡናዋም አሰናክሎ ቤት አስቀመጣት። ወደ Healing Valves Ethiopia የመጣችው ይህቺዉ ታዳጊ ከቶንሲል ጋር ተያይዞ የሚመጣው የልብ በር በሽታ (Rheumatic Heart Disease, RHD) አንዱን የግራ የልብ በሯን ክፋኛ ጎድቶት ነበር(Sever Mitral Valve stenosis and regurgitation) ለገና ስጦታ አንድ ህይወት ላድን ያሉ አንድ ለጋስ ግለሰብ የHVE የአገር በቀል የልብ ቀዶ ጥገና ቡድንን ተማምነው ባበረከቱት ስጦታ 4 ሰአት የፈጀው የግራ የልብ በር ቅየራ በድል ተጠናቋል። ታካሚያችን በመልካም ሁኔታ እያገገመች ሲሆን እኛም 26ኛውን የHVE በረከታችንን እነሆ ብለናል። 27ኛውም ይቀጥላል