ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ,Healing Valves Ethiopia (HVE) 27ኛውን የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አከናወነ እንደ Erling Braut Haaland በሳምንት $500,000 ባይከፈላቹም ወይም አካውንታቹ ሞልቶና ተትረፍርፎ እንደ ጢስ አባይ ባይንፎለፎልም ከተቸገሩ ወገኖቻችን ጋር አብረን እንቸገራለን ባላቹ ልዩ ልዩ ወገኖቻችን ባደረጋችሁት ድጋፍ, HVE 27ኛውን የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና በዛሬው እለት ለ13አመቷ የራያ ቆቦ ታዳጊ አከናውኗል.
ታዳጊዋም 4ሰአት ከፈጀው የግራ የልብ በር ቅየራ በኌላ በመልካም ሁኔታ እያገገመች ሲሆን, እባቷም ቄስ ሞላ እድሜዬን ሙሉ ያከበርኩት አምላክ ክሶኛል በማለት መሳቅ ጀምረዋል. ከቶንሲል ጋር ተያይዞ የሚከሰተው የልብ በር በሽታ (Rheumatic Heart Disease) እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ድሀ ሀገራት ላይ በአመት እስከ 300,000 ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል. ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያም ይህንን የታዳጊዋች በሽታ ከሀገራችን ለማጥፋት የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና በማድረግ ህብረተሰቡን በማንቃት ላይ ይገኛል.
እናንተም የ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በመሆን የዚህን ታሪካዊ ጉዞ አካል ይሁኑ. ልዩ ምስጋና፣ 1.የኪስ ቦርሳም ሆነ አካውንት ለሌላቹ ለፈለገሰብ ት/ቤት ተማሪዋች 2.ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ወርሀዊ የ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ መዋጮ በማድረግ ለምትደግፋን አባላት 3.የረመዳን ሰደቃውን ለሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ላደረገው Imran Shemsu Kemal ደም ከመለገስ ባሻገር ሂሊንግ ቫልቭስ
ኢትዮጵያን ማገዝ ህይወት ያድናል.