MERON – HVE 25th patient
Patient Story
September 28, 2025
በዛሬዉ እለት Healing Valves Ethiopia (HVE) 25ኛዉን የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ያከናወነ ሲሆን አራት ሰአት የፈጀዉ ይህ ቀዶ ጥገና አንደኛዉን የግራ ልብ በር በመቀየር (Mitral Valve Replacement) በሰላም ተጠናቋል። በቶንሲል ምክንያት በሚከሰተዉ የልብ በር በሽታ (Rheumatic Heart Disease) የተጎዳችው የ15 አመቷ ታዳጊ ሙሉ በሙሉ ነቅታ በመልካም ሁኔታ ላይ ትገኛለች። እንጀራ በመጋገርና እየተዘዋወረች ልብስ በማጠብ አራት ልጆች ማሳደግ ሳያንሳት የ15 አመቷ ሴት ልጇ ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚከሰት የልብ ህመም ልታጣት ቢሆንባት ነበር ወደ HVE የመጣችው። ያለአባት ያደገችው ሜሮንም በዚሁ በሽታ ምክንያት ትምህርቷን ከ5ኛ ክፍል ላይ ለማቋረጥ ተገደደች። የዚችን ድሀ የአድኑኝ ጥሪ ወጪ የሸፈኑት የHVE የሁልግዜም ቀኝ እጅ የሆኑት ሀሩን ከድር እና ሳምኤል ሀይሉ ናቸዉ። በሁለተኛ አመት ምስረታ በአላችን በሳምኤል ሀይሉ የተበረከተውን ስእል በጫረታ በመግዛት ለዚህች ህይወት መዳን ምክንያት ሆኗል። እኛም የሂሊንግ ቫልቭስ የልብ ቀዶ ጥገና ቡድን 25ኛውን የነፃ ልብ ቀዶ ጥገና በስኬት እነሆ በረከት ብለናል. በቶንሲል ምክንያት የሚመጣውን የልብ በሽታን (RHD) ለመቀነስና ለማጥፋት Healing Valves Ethiopiaን እናግዝ። ዛሬ የታመሙ ልቦችን እያዳን የነገ የልብ ታማሚዋችን እናጥፋ