በዛሬዉ እለት Healing Valves Ethiopia (HVE) 22ኛዉን የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ያከናወነ ሲሆን አራት ሰአት የፈጀዉ ይህ ቀዶ ጥገና አንደኛዉን የግራ ልብ በር በመቀየር (aortic valve replacement) በሰላም ተጠናቋል።
በቶንሲል ምክንያት በሚከሰተዉ የልብ በር በሽታ የተጎዳችዉ የ17 አመቷ ታዳጊ ሙሉ በሙሉ ነቅታ በመልካም ሁኔታ ትገኛለች።
እቀፋን ደግፋን የምንላቹህ እኛ የሀገር በቀል የHVE ቡድን በቀጣዩ እሁድ ነሀሴ 14, 2015 የ2ኛ አመት ምስረታ በዓላችን በAZEMAN Hotel ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ይከበራል።
ዛሬ የታመሙ ልቦችን እያዳን
የነገ የልብ ታማሚዋችን እናጥፋ
Let us eradicate RHD by raising awareness through healing of those severely affected by the disease.