MUSTAFA – HVE 15th patient

MUSTAFA – HVE 15th patient

በዛሬው እለት ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮዽያ (HVE) 15ኛውን የነፃ የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና ከአሳሳ አካባቢ ለመጣው የ17 አመት ወጣት በተሳካ ሁኔታ አካሄደ:: ትምህርቱን ከ4ኛ ክፍል በልብ ድካም ምክንያት ለማቋረጥ የተገደደው ታዳጊ; ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚከሰት የልብ በር በሽታ (RHD) ከ10 አመት በላይ በክትትል እና ቀጠሮ ኖሯል:: ለገና ስጦታ በተበረከተ በአንዲት ልበ ቀና የገንዘብ ልገሳና በ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮዽያ (HVE) የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አድራጊ ቡድን ክፋኛ የተጎዳውን የልብ በር ቅየራ (mitral valve replacement) በዛሬው እለት አከናውኗል::
እኛስ በሙያ እውቀታችን በጎ አደረግን ነገር ግን ካለ አንቺ ልገሳ ይህንን የገና ስጦታ የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና ባልተከናወነ ነበር:: ባለሀብት ሳትሆኝ ባለፅጋ መሆንሽን አስመሰከርሽ:: እናመሰግናለን::

Here is Healing Valves Ethiopia (HVE) gift for Christmas

Healing Valves Ethiopia (HVE) performed today the 15th free life-saving open-heart surgery for a 17 years old boy from Assasa. The boy was affected with Rheumatic Heart Disease (RHD), which led him to recurrent heart failure. He spent 10 years on follow up waiting for heart surgery and ultimately obliged the boy not to progress from grade Four. With the help of a solo person financial support for Christmas gift and the volunteer services of HVE, the severely damaged mitral valve was replaced in a four hours taking surgery.
Our free service of HVE and this life-saving heart surgery would not have been possible with out your generous support. You are not only a simple well to do person but also a kind hearted meaningful citizen. Thank you.