NEIMA – HVE 30th patient

NEIMA – HVE 30th patient

30 የሆነው በልፋት ነው. የ25ሚሊዮን ብር ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና 30ኛው የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ(HVE) አከናወነ. የ18 አመቷ የአ/አበባዋ ልጃገረድ ከ800,000-900 000 ሺ ብር የሚጠይቀውን የልብ በር ቅየራ ቀዶ ጥገና (Mitral Valve Replacement) ከHVE ተለግሳለች። አራት ሰአታት በፈጀው አንድ የግራ ልብ በር ቀዶ ጥገና በቶንሲል ምክንያት ክፋኛ የተጎዳው የታዳጊዋ የልብ በር ተቀይሯል፣ ታዳጊዋም ከሰመመን ነቅታ በማገገም ላይ ትገኛለች። አንድ ብሎ በጋቢ ህይወት የጀመረው የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የሚሰጠው የነፃ የልብ በር ቀዶ ጥገና አገልግሎት 30 ከመድረሱ ባሻገር፣ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎቻችን በተግባር የተደገፈ የRheumatic Heart Diseaseን መከላከያ መልእክት ያስተላለፈ ይገኛል። በቀጣይም በዚህ የልብ በር በሽታ ተጠቅተው በስቃይ ላይ ያሉ ታዳጊዎችን እያዳንን የመከላከያ ግንዛቤ እንድንፈጥር ከሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ጎን ይቁሙ