የናቷን የ40 ቀን የሙት መታሰብያ ህይወት በማዳን የዘከረች.
ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገችው ወ/ሮ ፋና እናቷን(ዚየን ታዬ) ከ40ቀን በፊት ባልተጠበቀ ሁኔታ በሞት ተነጥቃ በሀዘን ውስጥ ሆና ነበር ከHealing Valves Ethiopia (HVE) ስለአንዲት አሳዛኝ ወጣት የድረሱልን መልክት የተመለከተችው. የናቴ ሀዘን ማፅናኛ ይሁነኝም ስትል ያንበሳውን ድርሻ በመሸፈን HVE 16ኛውን የህይወት አድን የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና እንዲከውን አድርጋለች.
ከሆስፒታል በር ላይ እንባዋን ስትዘራ ልቡ የተነካ ሾፌርም እኛ ዘንድ በማቅረብ ትልቁን የህይወት ማዳን ስራ ሰርቷል.
እኛም የአገር በቀል የHVE የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አድራጊ ቡድን ይህንን ከባድ ሀላፊነት በድል ተወጥተናል.