SYMBONEY – HVE 28th patient
Patient Story
September 28, 2025
ሲምቦኔ፣ 28ኛ የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የነፃ የልብ ቫልቭ ቀዶ ጥገና ከብዙ ደጅ መጥናት ወድያ ፣ የሚጠበቅብን የሆስፒታል ክፍያ ባይሞላልንም ፣ በተለመዱ የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ቀኝ እጆች እርዳታ፣ በመቀጠልም የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የነፃ የበጎ አድራጊዎች አገልግሎት የጅማዋን ህፃን እንዲሁም ቤተሰቧን በዛሬው እለት ከስቃይ ገላግለናል። አራት ሰአታት በፈጀው አንድ የግራ ልብ በር ቀዶ ጥገና በቶንሲል ምክንያት ክፋኛ የተጎዳው የሲምቦኔ የልብ በር የተቀየረ ሲሆን፣ ታዳጊዋም ከሰመመን ነቅታ በማገገም ላይ ትገኛለች። አንድ ብሎ በጋቢ ህይወት የጀመረው የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ከሚሰጠው የነፃ የልብ በር ቀዶ ጥገና አገልግሎት ባሻገር፣ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎቻችን በተግባር የተደገፈ የRheumatic Heart Diseaseን መከላከያ መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ በቀጣይም በዚህ የልብ በር በሽታ ተጠቅተው በስቃይ ላይ ያሉ ታዳጊዎችን እያዳንን የመከላከያ ግንዛቤ እንድንፈጥር ከሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ጎን ይቁሙ።