YORDANOS – HVE 10th patient

YORDANOS – HVE 10th patient

እንደ ግለሰብም እንደ ሀገርም ሁላችንም የመምህሮቻችን ውለታ አለብን:: የዛሬው የ14 አመቱ የHVE የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ተጠቃሚ ታዳጊ ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚከሰተው የልብ በር ጉዳት ለአመታት ሲማቅቅ; መምህር አባቱ ለልጃቸው መፍትሄ የሚሆነውን የልብ ቀዶ ጥገና መላ ማበጀት አልቻሉም ነበር:: በልጁ የልብ ህክምና ችግር ከሚያስተምርበት ደራ ከምትባል ከተማ ወደ አ/አ የተሰደደው አባት ወደ HVE ቢሮ ድረስ በመምጣት ልጄን አድኑልኝ በማለት ተማፅነዋል::
በመሆኑም የHVE የ1ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ የአንድ ታዳጊ የልብ ህክምና ሙሉ ወጭ እሸፍናለሁ ያሉትና በቃላቸው የተገኙት አቶ ወሰን የለህ ዲታ ከ310,000 ብር በላይ በመርዳት የዚህን ታዳጊ የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና በዛሬው እለት እንድናካሂድ አድርገዋል::
የሀገር በቀል የHVE የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ቡድንም በግራ የልብ (mitral valve) በር ክፋኛ ያፈስ የነበረውን (regurgitation ) አንድ የልብ በር በተሳካ ሁኔታ መጠገን (mitral valve repair) ችለናል::
የ10ኛ የHVE የነፃ ልብ ቀዶ ጥገና ስኬት በማስመልከትም እኛ የHVE VOLUNTEER የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ቡድን ሾርባ ችርስ ቁጥር 2 አካሂደናል::